
ባሕር ዳር: ኅዳር 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ቀጣይ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ከቡርኪና ፋሶ ማክሰኞ ኅዳር 11 ጨዋታቸውን ለማከናወን ዝግጂት እያደረጉ ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጨዋታ ሰዓት ላይ ለውጥ እንዲደረግ ለፊፋ ጥያቄ አቅርቦ ነበር። ይህንን ተከትሎ ጨዋታው የሚደረግበት ሰዓት ቀድሞ ከነበረበት ምሽት 4፡00 ወደ ቀን 10፡00 መለወጡን ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!