
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ31 ሚሊየን ብር የቀዶ ሕክምና ቁሳቁስ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል ድጋፍ አድርጓል፡፡
የባንኩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር)÷ባለፈው ዓመት በማዕከሉ ጉብኝት ካደረጉ በኋላ ማዕከሉ ብቁ የሕክምና ባለሙያዎች እያሉት የቁሳቁስ እጥረት እንዳለበት መገንዘባቸውን አስታውሰዋል፡፡
በዚህ ሳቢያም ማዕከሉ ከአቅም በታች እንዲሰራ መገደዱን ተረድተው ችግሩን ለመቅረፍ ቃል ገብተው እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡
በተገባው ቃል መሰረትም ባንኩ በዛሬው ዕለት ለማዕከሉ 31 ሚሊየን ብር የቀዶ ሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
ድጋፉ ከ250 በላይ የልብ ቀዶ ሕክምናዎችን መሥጠት እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡
በድጋፉ በልብ ሕመም የሚሰቃዩ እና ወረፋ የሚጠብቁ ታካሚዎች እፎይታ ያገኛሉ መባሉንም የማዕከሉ መረጃ ያመለክታል ፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!