
ጎንደር: ኅዳር 7/2016 ዓ.ም (አማኮ) “ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ የእኛን ዘመን ጎንደር እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ ከጎንደር ከተማ ወጣቶች ጋር ዉይይት እየተደረገ ነዉ።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ ለጎንደር ከተማ የገቢ ምንጭ ከኾኑት አንዱ የቱሪዝም ዘርፍ ነዉ ብለዋል። ዘርፉ አሥተማማኝ ሰላም የሚፈልግ በመኾኑ ሁሉም ዜጋ ለሰላም ሊሠራ ይገባል ብለዋል። ሀገር ዘላቂ ሰላም እንዲኖራት የወጣቱ ሚና ከፍተኛ ነዉ የሚሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባዉ ወጣቶች ለሰላም መሥራት አለባቸዉ ነው ያሉት።
በመድረኩ የተገኙት በአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማእረግ የርእሰ መሥተዳድሩ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ ይርጋ ሲሳይ፤ በሰላም እጦት ምክንያት የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተቋርጠዋል ብለዋል። የተጀመሩ መሰረተ ልማቶች እንዲጠናቀቁም ወጣቶች ለሰላም ዘብ መቆም አለባቸው” ብለዋል።
የመንገዶች መዘጋጋት ለጤና ተቋማት የሚያሥፈልጉ የመድኃኒት እና ቁሳቁሶችን ለማቅረብ እና ወደ ከተሞች ሸቀጦችን ለማስገባት እንቅፋት ፈጥሯልም ብለዋል።
ለወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራም ሰላም አሥፈላጊ በመኾኑ ወጣቶች ለዘላቂ ሰላም ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።
ዘጋቢ: አዲስ ዓለማየሁ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!