
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አሥተዳደር በየደረጃው ያሉ መሪዎች በቀጣይ በአንድ ወር በኅብረተሰቡ ተሳትፎ በሚከናወኑ እቅዶች ዙሪያ ተወያይተዋል ።
ለውይይቱ ተሳታፊዎች መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ እንደገለፁት አሁን በከተማዋ በተገኘው አንፃራዊ ሰላም በመጠቀም በኅብረተሰቡ ተሳትፎ የልማትና የመልካም አሥተዳደር እቅዶችን ለማከናወን በትኩረት ይሠራል ።
በቀጣይ ትኩረት ከሚሰጥባቸው ተግባራት መካከል በኢኮኖሚው ዘርፍ የተጀመሩ መሠረተ ልማቶችን ማጠናቀቅ ፣ የግብርናና የእንሰሳት ሀብት ፣ ገቢ ማሰባሰብ ፣የሥራ እድል ፈጠራ ሥራዎች በትኩረት ይሠራሉ ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል ።
ከተማ አሥተዳደሩ በማህበራዊ ዘርፍ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ፣የወባ በሽታ ስርጭትን መከላከል ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት መሆናቸውን አስታውሰዋል ።
ከመልካም አሥተዳደር ሥራዎች አኳያ ደግሞ የዋጋ ማረጋጋት ሥራዎች ማከናወን ፣ የማኅበረሰብ አቀፍ የወንጀል መከላከል ሥራዎችን ማከናወን የመንግሥት ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል ትኩረት የተሰጣቸው እቅዶች መሆናቸውን ከንቲባው ገልጸዋል ።
በከተማ አስተዳደሩ ለሚከናወኑ ለታቀዱ እቅዶች ለማሳካት የተቀናጀ የኅብረተሰብ ተሳትፎ ማሳደግ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ከንቲባው ገልጸዋል ።
እቅዶችን ለማሳካትም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በትኩረት መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል ።
የፖለቲካና የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎችን አስመልክቶ የመወያያ ፅሁፍ በጎንደር ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋ መኮንን ቀርቧል።
የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ሥራዎችን በተገቢው መንገድ መሠራት እንደሚገባ አቶ ተስፋ ተናግረዋል ።
መረጃው የጎንደር ከተማ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!