የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅሬታውን ለፊፋ አቀረበ።

54

ባሕር ዳር: ኅዳር 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በትናንትናው ዕለት በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከሴራሊዮን ጋር ተጫውቶ ያለ ጎል አቻ መለያየቱ ይታወሳል።

ጨዋታው በጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ለእይታ አስቸጋሪ በመኾኑ ሁለተኛው አጋማሽ መጀመር ከነበረበት 30 ደቂቃዎች ያህል ዘግይቶ ጀምሯል።

በሁለተኛው አጋማሽ ለተጨማሪ ሁለት ጊዜያትም ተቋርጦ ነበር።

ይህን አስመልክቶ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቅሬታውን ለፊፋ አሳውቋል። በዚህ የአየር ሁኔታ ጨዋታ እንዲቀጥል መደረጉ አግባብ አልነበረም ብሏል።

ጨዋታው ለቀጣይ ጊዜ መተላለፍ ቢኖርበትም እንዲቋረጥ አለመደረጉ ፍትሃዊ እንዳልኾነ በደብዳቤ ቅሬታውን እንደገለጸ ፌዴሬሽኑ አሳውቋል።

በተያያዘ መረጃ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቀጣይ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የሰዓት ለውጥ እንዲደረግ ለፊፋ ጥያቄ አቅርቧል።

ፊፋ ጉዳዩን እየተመለከተ እንደሆነ እና በፍጥነት ምላሽ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከታተሙ መጻሕፍት ውስጥ 56 በመቶ ትምህርት ቤቶች ላይ ደርሰዋል” የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
Next articleአፈ-ጉባዔ አገኘሁ በቻይና የብሔራዊ ሕዝብ ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ።