
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የመንግሥት ሠራተኛ መሰረታዊ ድርጅት ኮንፈረንስ አካሂደዋል፡፡
ኮንፈፍረንሱ እየተገኘ ያለውን ሰላም በማፅናት ላይ የመሠረታዊ ድርጀት አባላቱ ስለሚኖራቸው ሚና እና በቀጣይ የ90 ቀናት የፓርቲ ሥራዎች ዕቅድ ላይ በትኩረት መክሯል፡፡ የተጀመረውን የአመራር ሪፎርም ሥራ በማጠናከር ጥራት ያለው
አመራር በአመለካከትና በተግባር የመገንባቱ ሥራ ስለማጠናከርና የአባላቱ ሚና ምንነት ላይ በውይይቱ በስፋት ተነስቶ ምክክር ተደርጎበታል። በውይይትና በመግባባት እንጂ በአፈሙዝ የሚፈታ የሕዝብ ጥያቄ ባለመኖሩ በሁሉም ችግሮቻችን ዙሪያ በመወያየት በተቀመጠው የመፍትሔ አቅጣጫ ላይ በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅም ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡ መረጃው የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!