
አዲስ አበባ: ኅዳር 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከ2 ቢሊዬን ዶላር በላይ የሚያወጣ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በቀጣይ 5 ዓመታታት የኔትወርክ ዝርጋታና የአገልግሎት ማስፋፊያ ለመሥራት አቅዶ እየሠራ እንደሚገኝ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ገልጿል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄሌፑት በቀጣይ አምስት ዓመታት እስከ 12 ሺህ የሚደርሱ የኔትወርክ ማማዎችን በመላው ኢትዬጵያ እንተክላለን ብለዋል። አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ እየሠራ ስለመኾኑም ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አሥፈጻሚው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ማፍራቱን ጠቁመዋል። በ26 ዋና ዋና ከተሞች እና በ254 ትናንሽ ከተሞች የቴሌኮም አገልግሎቱን እያቀረበ እንደሚገኝም ዋና ሥራ አሥፈጻሚው ተናግረዋል።
ሳፋሪኮም አዳዲስ ልምዶችን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት በቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጥራት፣ ተደራሽነት እና ፈጠራ ላይ የተሻሉ ውጤቶችን ለማምጣት በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ዋና ሥራ አሥፈጻሚው ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ቤቴል መኮንን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!