
ደሴ: ኅዳር 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች በወቅታዊ የልማት እና የፀጥታ ጉዳዩች ዙሪያ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን እና የክልሉ የብልፅግና ፓርቲ የፓለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ተፈራ ፍቅሩ (ዶ.ር) በተገኙበት እየተወያዩ ነው።
በውይይቱ ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የኮምቦልቻ ማኅበረሰብ ከመሪዎች ጋር በመተባበር ሰላሙን ለማስጠበቅ ያደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን ሰላምን በዘላቂነት ለማስፈን የኅብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኚነት አለው ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊወች ስለ ሰላም አሥፈላጊነት፣ ስለ ኑሮ ውድነት፣ ስለ ሥራ እድል ፈጠራ፣ ስለ ግብር አወሳሰን እና ፍተሐዊነት አንስተዋል።
የሚነሱ የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ በማቅረብ ከኅብረተሰቡ ጋር ተቀራርቦ በመሥራት መፍትሔ መስጠት እንደሚገባ በመድረኩ ተነስቷል።
ዘጋቢ፡- አበሻ አንለይ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!