ጎጃም በሚገኙ ሁሉም ዞኖች ያለው የሰላም ኹኔታ ከፍተኛ መሻሻሎች እያሳየ መኾኑን ኮማንድ ፖስቱ አረጋገጠ።

79

ባሕር ዳር: ኅዳር 5/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጎጃም በሚገኙ ሁሉም ዞኖች ያለው የሰላም ኹኔታ ከፍተኛ መሻሻሎች እያሳየ መኾኑን ኮማንድ ፖስቱ ማረጋገጡን አስታውቋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት የዕቅድ አፈጻጸሙን በደብረማርቆስ ከተማ በገመገመበት ዕለት እንደተገለጸው ፣ በጎጃም ባሉ ሁሉም ዞኖች እና ከተሞች በተሠራው ሕግ የማስከበር ሥራ ለውጥ ታይቷል ።

በአማራ ክልል በምክትል ርእሰ መሥተደድር ማዕረግ የመልካም አሥተዳደር ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው እንዲሁም የምሥራቅ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ተሰማ እንደተናገሩት ፣ ሠራዊቱ

በተሰማራባቸው ሁሉም አካባቢዎች የመንግሥት መዋቅር መልሶ በመደራጀት ላይ ይገኛል ። ፖሊስ፣ ሚሊሻ እና ሌሎች አካላት ከመከላከያ ጋር ተሰልፈው ግዳጅ እየተወጡ እንደሚገኙ ተገልጿል። የጽንፈኛው ቡድንም ከሕዝብ እየተነጠለ መጥቷል የሕዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትም ሥራ ጀምረዋል ።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ሰላሙ ቀጣይ እንዲኾን የፖለተካ አመራሩ የሕዝብ ግንኘነት ሥራ በማጠናከር፣ የፖሊስ፣ የሰላም ማስከበር እና የሚሊሺያ አባላትን በማደራጀት፣ የሕዝብ አገልግሎትን በተደራጀ መንገድ በመምራት ከሠራዊታችን ጎን በመኾን የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ የዓመቱን የመማር ማስተማር ሂደት ለማሻሻል ጥናት እየተደረገ ነው ተባለ።
Next article“አርሶ አደሮች ሲፈልጉን መገኘት ይገባናል” አጀበ ስንሸው የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ