
ባሕር ዳር: ኅዳር 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ለ2026ቱየዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያውን የምድብ ጨዋታ ከሴራሊዮን ጋር ያካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ያለምንም ግብ በአቻ ውጤት ጨዋታውን ጨርሷል።
በሞርኮው ኤል-አብዲ ስታዲየም በነበረ ከፍተኛ የጭጋግ ሽፋን ውስጥ የተካሄደው ጨዋታ እረፍት ሰዓት ላልተወሰነ ጊዜ ለማቋረጥ ተገዶ ነበር።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ የዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ ምሽት 4:00 በተመሳሳይ በሞርኮው ኤል-አብዲ ስታዲየም ከቡርኪናፋሶ ጋር ያደርጋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!