
ባሕር ዳር: ኅዳር 5/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በቻይና ብሔራዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር ሎሳንግ ጂያልትሰን የተመራ የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገባ።
የልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ አቀባበል አድርገውለታል።
ኢዜአ እንደዘገበው የልኡካን ቡድኑ በቆይታው ከምክር ቤት አባላትና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!