ዋልያዎቹ ዛሬ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሴራሊዮን ጋር ይጫዎታሉ።

62

ባሕር ዳር: ኅዳር 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከሴራሊዮን ጋር የሚያደርገው የመጀመርያ ጨዋታ ዛሬ በሞሮኮዋ ኤል-ጀዲዳ ከተማ በሚገኘው ኤል-አብዲ ስታዲየም ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከናወናል።

በዛሬው ጨዋታ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አረንጓዴ ማልያ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ ለብሶ ወደ ሜዳ ሲገባ ሴራሊዮን ሙሉ ነጭ መለያን ትጠቀማለች።

ጨዋታውን ሞዛምቢካዊው አልቫሲዮ ሴልሶ ከአንጎላዊያን ረዳት ዳኞች ጄርሰን ኤሚሊያኖ እና ኢቫኒልዶ ኦ ሳንቾ እንዲሁም ሞዛምቢካዊው አራተኛ ዳኛ ጉዋምቤ በርናርዶ ጋር ይመራዋል።

ደቡብ ሱዳናዊው ራሳስ ሊብራቶ ደግሞ በኮሚሽነርነት መመደባቸውን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የጋራ ብሔራዊ ትርክት መገንባት ተገቢ ነው” አደም ፋራህ
Next articleየቻይና ብሔራዊ ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር ሎሳንግ ጂያልትሰን አዲስ አበባ ገቡ።