
ባሕር ዳር: ጥቅምት 3/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በእንጅባራ ከተማ ወቅታዊ የሰላም ጉዳዮች ላይ ሕዝባዊ የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በሰላም ውይይቱ ላይ የእምነት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
እንጅባራ ከተማ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሰላማዊ ቤት ናት ሲሉ ተናግረዋል። “እንጅባራ በሰላም ወዳድ ነዋሪዎቿ ሰላሟ ይጠበቃል” ሲሉም ገልጸዋል ነዋሪዎቹ።
ሁሉም የእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች ሰላም ወዳድ እና ሕዝብን ለመበጥበጥ ፍላጎት ላላቸው የፖለቲካ ነጋዴዎች የማንመች ነን ሲሉ ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፖለቲካ ቁማር እና በግጭት የራሳቸውን ትርፍ አስልተው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እና ፖለቲከኞች የእንጅባራን ሰላም ለማወክ ሲንቀሳቀሱ ቢስተዋልም ሊሳካላቸው ግን አልቻለም ተብሏል።
አሁን ላይ በከተማዋ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንደሌለ እና ነዋሪዎችም በሰላም እና በነጻነት የሚሠሩባት ከተማ ናት። ከተማዋ ሁሉን በፍቅር፣ በአብሮነት እና በመተሳሰብ ለዘመናት የሚኖርባት ናት ያሉት የሀገር ሽማግሌዎች ይህንን ሰላም ለማስቀጠል ነዋሪዎች ሁሉ በላቀ ትጋት ለሰላማቸው ዘብ መቆም አለባቸው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!