
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት በነገው ዕለት ያካሂዳል።
ምክር ቤቱ 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ሌሎች የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የሕግ አስፈጻሚውን አካል አሠራር የመመርመር ሥልጣን እንዳለው በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ 17 ተደንግጓል፡፡
በዚህ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በነገው የምክር ቤቱ ጉባኤ ላይ በመገኘት ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ መስከረም 28 ቀን 2016 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ያቀረቡትን የፌደራል
መንግስቱን ዓመታዊ ዕቅድ የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤት አባላት ለሚነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ የሚሰጡ ይህናል።
ምክር ቤቱ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በነገው ዕለት በሚካሄደው የምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባ የሃይማኖት አባቶች ተወካዮች፣ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ተጠሪዎች፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!