“ላሊበላ ጉዳት ደረሰበት በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሠረት ቢስ ነው” የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ

61

ባሕር ዳር፡ ኅዳር 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቀደምት ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስ ነው። የክልላችን ሃብት፣ የሀገራችን ኩራትና ኢትዮጵያዊያን የቀደምት ስልጣኔ ባለቤቶች መሆናችን ማሳያ መኾኑን ቢሮው ገልጿል።

በዚህ የዓለማችን ቀደምት ቅርስ ስም ሐሰተኛ ፕሮጋንዳ እየነዙ፤ ሕዝብን እያደናገሩ አሸናፊ ለመሆን መሞከር ሞራላዊና ኅሊናዊ ኪሳራን እንጅ ድልን አያጎናጽፍም ብሏል ቢሮው በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ባጋራው መረጃ።

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በሚገኘው የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተደርጎ ከትናንት ጀምሮ የሚናፈሰው ወሬ መሠረት ቢስ ነው።

በላሊበላ ስም መቀደስ እንጅ የጥፋት ድግስ መደገስ አስፈላጊና ተገቢ አይደለም። የላልይበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቦታውም ቅዱስ ነው ህንጻውም ሰላም ነው ብሏል ቢሮው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ማይካድራ፡- የማይረሱ ቀኖች፤ የማይዘነጉ ግፎች” 
Next article“የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የቱሪዝም ገቢ ለማሳደግ ያግዛሉ” የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር