
ባሕር ዳር: ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ኢትዮጵያ ከሳውዲ – አፍሪካ ጉባዔ ጎን ለጎን ከጂቡቲ እና ሶማሊያ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሳዑዲ – አፍሪካ ጉባዔ ጎን ለጎን ከጂቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ እና ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼህ ሞሃመድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ከሳዑዲ – አፍሪካ ጉባዔ ጎን ለጎን ከወንድሞቼ የጂቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ እና የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼህ ሞሃመድ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!