
ባሕር ዳር: ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የመጡ የመንግሥት አመራሮች ሥልጠና በባሕር ዳር የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።
ከልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሥልጠና ወደ አማራ ክልል የገቡ መሪዎች አቀባባል እንደተደረገላቸው መዘገባችን ይታወሳል። በክልሉ ዋና ከተማ ባሕር ዳር የሚሰጠው ሥልጠናም የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው።
በመሪዎች ሥልጠና የማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ የዲሞክራሲ ባሕል ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ መለስ ዓለም፣ የብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በየደረጃው የሚገኙ የሀገሪቱ የመንግሥት አመራሮች ለቀናት ሥልጠና እንደሚወስዱ ይጠበቃል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!