“የሕዳሴ ግድብ ቀጣናውን በልማት የሚያስተሳስር ግዙፍ ፕሮጀክት ነው” ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ

47

ባሕር ዳር: ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎበኝተዋል።

በጉብኝቱ የመከላከያ የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ የ47 ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች፤ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።

ሜጀር ጀነራል ተሾመ ገመቹ “የሕዳሴ ግድብ ቀጣናውን በልማት የሚያስተሳስር ግዙፍ ፕሮጀክት ነው” ብለዋል፡፡

የጉብኝቱ ዓላማም ወታደራዊ አታሼዎች ግድቡ ቀጣናውን በልማት ለማስተሳሰር ያለውን ፋይዳ እንዲሁም በታችኛው የተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉልህ ጉዳት እንደማያደርስ በአካል ተገኝተው እንዲመለከቱና እውነታውን እንዲረዱ ማድረግ ነው ብለዋል።

ግድቡ በኢትዮጵያውያን ገንዘብ እውቀትና ላብ እየተገነባ የሚገኝ አዲስ ብሔራዊ ኩራት መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የግፍ ደም የፈሰሰባት፣ የዘር ፍጅት የተፈጸመባት”
Next articleበብሔረሰብ አስተዳደሩ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ከ75 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለ፡፡