
ባሕር ዳር: ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሳዑዲ በኢትዮጵያ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን እንደምትደግፍ አረጋግጣለች፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከሳዑዲ አቻቸው መሐመድ አል ጅዳን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ውይይቱ በሪያድ እየተካሄደ ከሚገኘው የሳዑዲ ዓረቢያ- አፍሪካ ኢኮኖሚ ኮንፍረንስ ጎን ለጎን ነው የተደረገው፡፡
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ልማት እና እዳ ሽግሽግ ላይ መምከራቸውን በሳዑዲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!