በዩሮፓ ሊግ ዌስትሃም ከኦሎምፒያኮስ ዛሬ ይጫዎታል።

59

ባሕር ዳር: ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ዌስትሃም ዩናይትድ እና ኦሎምፒያኮስ በዩሮፓ ሊግ በምድብ አንድ የተደለደሉ ክለቦች ናቸው፡፡

ሁለቱ ክለቦች ዛሬ አራተኛ ጨዋታቸውን 80 ሺህ ተመልካች በሚይዘው በለንደን ስታዲየም ያደርጋሉ፡፡

ዌስትሃም ሦሥት ጨዋታዎችን አድርጎ በስድስት ነጥብ በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

አሠልጣኝ ዴቪድ ሞይስ ኦሎምፒያኮስ በጣም ጥሩ ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾች እንዳሉት አምነዋል፡፡ ነገር ግን ከሁለት ሳምንት በፊት በግሪክ ከደረሰባቸው ሽንፈት ተምረው ዛሬ ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡

አሠልጣኝ ሞይስ 4-3-3 የቡድናቸው አሰላለፍ እንደሚኾን ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ሜይል ኦንላይን እንዳስነበበው የሞይስን አስተያየት “የፍራቻ ነው” ሲል ገልጾታል፡፡

ዌስትሃም በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግም 11 ጨዋታዎችን አድርጎ አራት ጨዋታዎችን አሸንፎ፣ በሁለቱ አቻ ወጥቶ እና በአምስቱ ተሸንፎ በ14 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ነው፡፡

በምድብ አንድ የዌስትሃም ተጋጣሚ ኦሎምፒያኮስ ሦሥት ጨዋታዎችን አድርጎ አንዱን አሸንፎ፣ በአንዱ አቻ ወጥቶ እና በአንዱ ተሸንፎ በአራት ነጥብ ሦሥተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ይህን ጨዋታ ካሸነፈም ዌስትሃም በአንድ ነጥብ ይበልጠዋል፡፡

ኦሎምፒያኮስ እየሠለጠነ የሚገኘው በአሠልጣኝ ዲያጎ ማርቲኔዝ ነው፡፡ እሳቸው እንደሚሉት በ2024/25 የውድድር ዘመን ክለባቸው በ100ኛ ዓመት ዋዜማው ላይ ኾኖ የሀገራቸውን ሊግ እና የዩሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ለማንሳት ተስፋ ሰንቋል፡፡

ማርቲኔዝ ኦሊምፒያኮስ ሁልጊዜ ማሸነፍን ግቡ ያደረገ ቡድን ነው። የምንችለውን ኹሉ ለማድረግ እየተጠባበቅን ነው ብለዋል።

በተጫዋቾቼ እና በቡድኑ አባላት አቅም ከፍተኛ እምነት አለኝ ያሉት አሠልጣኙ በዛሬው ጨዋታም ዌስትሃምን በድጋሚ በብቃት ለማሸነፍ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

ኦሊምፒያኮስ በአሁኑ ሰዓት በሱፐር ሊግ ግሪክ አንድ ሰንጠረዥ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ስሎቬንያዊው የመሐል ዳኛ ማትጅ ጁግ በለንደን ስታዲየም የሚካሄደውን ጨዋታ ይመሩታል።

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ ዳግም እንዳይከሰት ሁሉም ለሰላም ዘብ ሊቆም ይገባል” የማይካድራ ከተማ ነዋሪዎች
Next articleየመጀመሪያው ሀገራዊ የሳይበር ደኅንነት ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።