አቶ ደመቀ መኮንን የመቄዶንያ የአረጋውያን ማዕከልን ጎበኙ

62

አዲስ አበባ: ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የመቄዶንያ የአረጋውያን ማዕከልን ጎበኙ፡፡

ጉብኝቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የአረጋውያን ቀንን ምክንያት በማድረግ ነው፡፡

ቀኑ “የአረጋውያንን መብት ማክበር ትውልድን ማሻገር” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም አረጋውያን መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙና በወጡ ህጎች ተግባራዊነት ላይ የሚያተኩር የፓናል ውይይት እንደሚደረግም ይጠበቃል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የዩኒቨርሲቲ መማር ማስተማር ፍጹም ሰላምን ይሻል” የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ.ር)
Next article“የሳይበር ደኅንነት ጥናት እና ምርምሮች ከሀገር አቀፍ አልፈው ቀጠናዊ እና አህጉራዊ እንዲኾኑ እንሠራለን”