
ባሕር ዳር: ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል።
ምክር ቤቱ በሚያካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትን ይገመግማል። የግል ዳታ ጥበቃ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴም ይመራል።
የገጠር መሬት አሥተዳደርና አጠቃቀም እንዲሁም የልዩ ኢኮኖሚ ዞን ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ የሚመራ ይኾናል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!