የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬም ይቀጥላሉ።

52

ባሕር ዳር: ጥቅምት 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ሻምፒዮንስ ሊጉ በየምድቡ ጥሎ ማለፉን የሚቀላቀሉ ክለቦችን ለመለየት የምድብ ጨዋታዎችን እያካሄደ ነው።
ዛሬ ምሽት ከምድብ አንድ እስከ ምድብ አራት ያሉ ቡድኖች ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።
ከምድብ አንድ ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ዴንማርክ ተጉዞ ኮፐንሀገንን የሚገጥምበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። የድሮ አስፈሪነቱ የከዳው ዩናይትድ በሦስት ጨዋታ ሦስት ነጥብ ብቻ ሰብስቧል። ተጋጣሚው ኮፐን ሀገን በተመሳሳይ የጨዋታ ቁጥር አንድ ነጥብ ብቻ ነው ያሳካው። በዛሬው ጨዋታ የማለፍ ተስፋቸውን ከፍ ለማድረግ ጥሩ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።
በምድቡ ሌላ ጨዋታ የምድብ መሪዎቹ ባየርሙኒክ እና ጋላታሳራይ የሚገናኙ ይኾናል። ሙኒክ ምድቡን በዘጠኝ ነጥብ ሲመራ ጋላታሳራይ በአራት ነጥብ ይከተላል።
አርሴናል ሲቪያን በሜዳው የሚገጥምበት ጨዋታም በምሽቱ ትልቅ ግምት ከተሰጣቸው ጨዋታዎች መካከል ነው።
በዚሁ ምድብ ሌላ ጨዋታ የሆላንዱ ፒኤስቪ አይንዶቨን የፈረንሳዩ ሌንስን ይገጥማል። አርሴናል ምድቡን በስድስት ነጥብ እየመራ ነው።
ሪያል ማድሪድ ከስፖርቲንግ፣ ናፖሊ ከዩኔየን በርሊን ሲጫዎቱ፣ ሪያል ሶሲዳድ ከቤኔፊካ፣ ሳልዝበርግ ከኢንተር ሚላን ዛሬ የሚከናወኑ ጨዋታዎች ናቸው ሲል ቢቢሲ አስነብቧል።
ትናንት ምሽት በተደረጉ ጨዋታዋች ማንቸስተር ሲቲ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀበትን ውጤት አስመዝግቧል።
በሜዳው የተጫወተው ማንቸስተር ሲቲ የሲውዘርላዱን ያንግ ቦይስን 3 ለ 0 አሸንፏል።ይህን ተከትሎም የጋርዲዮላው ቡድን ጥሎ ማለፉን በመቀላቀል ቀዳሚ ኾኗል።
በሌሎች ጨዋታዎች አትሌቲኮ ማድሪድ ሴልቲክን በሰፊ ግብ አሸንፏል።የስፔኑ ክለብ ስድስት ግቦችን ነው በተጋጣሚው ላይ ያስቆጠረው።
በተጠባቂው የዶርትሙንድ እና ኒውካስትል ጨዋታ ደግሞ የጀርመኑ ክለብ ባለድል ኾኗል።
ዶርትሙንድ ጨዋታውን 2 ለ 0 ነው ያሸነፈው።
በዚሁ ምድብ ኤሲሚላንን ከፒኤስጂ ያገናኘው ጨዋታም በጣሊያኑ ክለብ አሸናፊነት ተጠናቅቋል።
ባርሴሎና በዩክሬኑ ሻካታር ዶኔስክ ሲረታ፣ የፓርቱጋሉ ፖርቶ የዴንማርኩን ሮያል አንትዋርፕን ማሸነፍ ችሏል።
የጣሊያኑ ላዚዮ የሆላንዱን ፌየኖርድ ፣ የጀርመኑ አርቢ ሊፕዚንግ የሰርቢያውን ሬድ ስታር ቤልግሬድን ማሸነፍ ችለዋል።
አሰማማው አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት አድርገናል” የወሎ እና የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች
Next articleአስተማማኝ የዳታ ሴንተር አገልግሎት በመስጠት ወጭ መቀነስ እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡