የአል ኢቲሃድ አሠልጣኙን አሰናበተ።

32

ባሕር ዳር: ጥቅምት 28/2016 (አሚኮ) የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ተሳታፊው አል ኢቲሃድ ፖርቹጋላዊውን አሰልጣኝ ኑኖስ ስፕሪንቶ ሳንቶስን ከአሠልጣኝነት አሰናብቷል፡፡

ኑኖስ ስፕሪንቶ ሳንቶስ የቶተንሃም ሆትስፐር እና የወልቭስ አሠልጣኝ የቀድሞ አሠልጣኝም ነበሩ። የሳዑዲ ፕሮ ሊግ ተሳታፊው አል ኢቲሃድ አሰልጣኝ ሳንቶስን ያሰናበተው ደካማ እንቅስቃሴ አሳይተዋል በሚል ምክንያት ነው።

አሠልጣኙ ከተካሄዱ 12 ጨዋታዎች በ6ቱ ብቻ ነው ያሸነፉት። አል ኢቲሃድ ባለፈው ሰኞ በእስያ ሻምፒዮንስ ሊግ በኢራቁ ኤር ፎርስ ክለብ 2 ለ 0 ተሸንፎ ከውድድሩ ተሰናብቷል፡፡

በዚህም አሠልጣኙ ከስምንት ወራት የኀላፊነት ቆይታ በኋላ አል ኢቲሃድ ጋር በይፋ ተለያይተዋል። ምክትል አሠልጣኙ ሀሰን ካሊፋ ቡድኑን በጊዜያዊነት ይመራሉም ተብሏል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጤፍን በኩታገጠም በመዝራታቸው እስከ 15 ኩንታል በሄክታር ይገኛል የሚል ተስፋ እንዳላቸው አርሶ አደሮች ገለጹ።
Next article“ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት አድርገናል” የወሎ እና የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲዎች