
ባሕር ዳር: ጥቅምት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በቻይና ሹቾ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
በወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት መልካ ደርቤ ቀዳሚ ኾኗል። በ2 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ ውድደሩን በማጠናቀቅ የቦታውን ሰዓት አሻሽሎ ነው ያሸነፈው።
በሴቶች የሹቾ ማራቶን ውድድር አትሌት ደራርቱ ሀይሉ በአንደኝነት አሸንፋለች። 2 ሰዓት ከ27 ደቂቃ ከ47 ሰከንድ በኾነ ሰዓት ነው ውድድሩን ያጠናቀቀችው፡፡ ከዚህ ቀደም የውድድሩ ሪከርድ የነበረውን 2 ሰዓት ከ29 ደቂቃ ከ47 ሰከንድ ከአንድ ደቂቃ በላይ ማሻሻሏን ፒፕልስ ዴይሊ ኦንላይን ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!