የዋልያዎቹ ሁለት ተጫዋቾች ከስብስቡ ውጭ ኾነዋል።

40

ባሕር ዳር: ጥቅምት 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ትላንት ዝግጅቱን ከጀመረው የዋልያዎቹ ስብስብ ውስጥ ሁለት ተጫዋቾች ከቡድኑ ውጭ መሆናቸው ታውቋል።

በአሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ በሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ለሰላሳ ተጫዋቾች ጥሪ ቀርቦላቸው ነበር። ጌታነህ ከበደ ራሱን ከብሔራዊ ቡድን ማግለሉን ተከትሎ ከስብስቡ ውጪ መኾኑ ሲረጋገጥ ሌሎቹ ሁለት ተጫዋቾች ከቡድኑ ስብስብ ውጭ መኾናቸው ታውቋል።

ከስብስቡ ውጪ ከኾኑት አንደኛው አጥቂው አቡበከር ናስር ሲኾን ምንም እንኳን ከህመሙ አገግሞ መጠነኛ ልምምድ ቢጀምርም ለቀጣዩ ሁለት ጨዋታዎች ለመድረስ የሚያስችል የአካል ብቃት ደረጃ ላይ የማይገኝ በመኾኑ ከቡድኑ ስብስብ ውጪ መደረጉ ተገልፆል።

ሌላው አማካይ ሽመልስ በቀለ ነው። በተመሳሳይ በሊጉ አምስተኛ ሳምንት መቻል ከሀንበሪቾ ጋር ባደረገው ጨዋታ በመጀመርያው አጋማሽ የጡንቻ መሳሳብ ጉዳት በማስተናገዱ ተቀይሮ መውጣቱ ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት ከዚህ ህመም ብዙ ባለማገገሙ ምክንያት ከብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ የኾነ ሌላኛው ተጫዋች ኾኗል።

እንደ ሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ዋልያዎቹ በዚህ ሰዓት 27 ተጫዋቾችን በመያዝ ሁለተኛ ቀን ልምምዳቸውን በአዳማ ዩኒቨርስቲ ሜዳ እየሠሩ ይገኛሉ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሸዋበር የደጋጎች መማጸኛ፤ የመሻይኮች መገናኛ”
Next articleኢትዮጵያውያን አትሌቶች በቻይና ሹቾ ማራቶን ድል ቀናቸው።