“በደብረ ብርሃን ከተማ በተሠሩ ሥራዎች በከተማው አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል” የከተማ አሥተዳደሩ

42

ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ የሚታዮ ችግሮችን ለመፍታት እና ስኬቶችን ለማስቀጠል የከተማ አሥተዳደሩ ከነዋሪዎቹ ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

ሕዝብ ሰላምን ይፈልጋል ፤ ይህ እንዲረጋገጥ ደግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች ላይ መንግሥት ምላሽ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል። ይህ ሲኾን ሕዝቡም በመንግሥት ላይ ያለው አመኔታ እና ተስፋ ይጨምራል ብለዋል።

የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብእሸት የሕዝቡን ጥያቄ ለመፍታት ሲባል የመሪዎች መልሶ የማዋቀር ሥራ እንደተሠራ አሳውቀዋል።

በተሠሩ ሥራዎች አሁን ያለው አንጻራዊ ሰላም እንደተገኘ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል። ይህንን ለማስፋት ሕዝቡ ከመንግሥት ጋር በተጠናከረ መንገድ ሊሠራ እንደሚገባ ተናግረዋል። ሰላሙ ከዚህ የተሻለ ሲሻሻል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንደሚነሳ ጠቁመዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ትኩረት ያጣውን የአኩሪ አተር ምርት ለተለያዩ የምግብ አይነቶች እንዲውል በማድረግ ተፈላጊነቱን ጨምረናል” የምዕራብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ
Next articleበኩር ጋዜጣ ጥቅምት 26/2016 ዓ.ም ዕትም