“በሦስት ወራት ከ13 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አግኝተናል” የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ

33

ባሕር ዳር: ጥቅምት 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ባለፉት ሦስት ወራት 13 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ በሩብ ዓመቱ በባሕር ትራንስፖርት አገልግሎት 971 ሺህ 438 ቶን ገቢ ጭነትና ከ200 ሺህ ቶን በላይ ወጪ ጭነት በባሕር ማጓጓዙ ተገልጿል፡፡

በጭነት አስተላላፊነት አገልግሎት በኩል 29 ሺህ 557 ኮንቴይነርና 411 ተሽከርካሪዎችን በመልቲሞዳል ስርዓት ወደ ሀገር ውስጥ ወደቦችና የጉምሩክ ፈቃድ ያላቸው መጋዘኖች ማድረስ መቻሉም ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም 832 ሺህ 70 ቶን ገቢ ጭነት እና 83 ሺህ 662 ቶን ወጪ ጭነት በዩኒሞዳል የትራንስፖርት ሥርዓት ማስተላለፍ መቻሉን ገልጿል።

በሩብ ዓመቱ በአጠቃላይ ለ104 ሺህ 659 ኮንቴይነሮች በወደብና ተርሚናሎች አገልግሎት መሰጠቱ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታውቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በአንድ ነጥብ ሦስት ቢሊዮን ብር የአየር ትንበያ አገልግሎት ማዕከል እየተገነባ ነው” የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት
Next article“የአፈር አሲዳማነትን ለመከላከል ዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታል ኖራ ለክልሎች ሊሰራጭ ነው” የግብርና ሚኒስቴር