መዲና ኢሳ በዓለም ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ምርጥ አትሌት ምርጫ ፍጻሜ ደረሰች።

58

ባሕር ዳር: ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም አትሌትክስ ፌዴራሽን የ2023 ከ20 ዓመት በታች ሴት አትሌቶችን ሦስት የፍጻሜ እጩዎችን ያስተዋወቀ ሲሆን፣ ኢትዮጵያዊቷ መዲና ኢሳ ከሦስቱ እጩዎች እንዷ ኾናለች፡፡

እጩዎቹ በዘንድሮው የወድድር ዓመት በቡዳፔስት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፣ በባቱርስት የዓለም አትሌቲክስ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና፣ በሪጋ የጎዳና ላይ ሩጫ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እና በሌሎች ውድድሮች ባሳዩአቸው አስደናቂ ብቃት እንደተመረጡ ፌዴሬሽኑ በገጹ አስታውቋል፡፡

መዲና ኢሳ በ2022/23 የውድድር ዓመት በዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ አሸናፊ፣ በ5 ሺህ ሜትር የዓለም ሻምፒዮና ስድስተኛ ደረጃ እና 14፡16፡54 የግሏን ምርጥ ሰዓት እንዲሁም የዓለም የጎዳና ሩጫ ሻምፒዮና በ5 ኪሎ ሜትር አራተኛ ደረጃ ወጥታ ማጠናቀቋ ለምርጫው አስተዋጽኦ እንዳደረገ ተጠቅሷል።

የ2023 ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ሽልማት አሸናፊ በዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ከተገመገመ በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.አ.አ ታኅሳስ 11 እንደሚገለጽ መረጃው ያመለክታል።

እንደ ኢቢሲ ዘገባ ከመዲና ኢሳ ጋር የሚፎካከሩት ኬኒያዊቷ ፌይዝ ቼሮቲክ እና ሰርቢያዊቷ አንጀሊና ቶፒክ ናቸው፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሕዝብ ጥያቄዎችን መፍታት እንዲቻል ሰክኖ ማሰብ፣ እድል መስጠት እና በአንድነት መቆም ይገባል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው
Next article“የሕዝብ ጥያቄዎች በሕግ ማዕቀፍ እንዲመለሱ የክልሉ መንግሥት እየሠራ ነው” አቶ ሲሳይ ዳምጤ