ርዋንዳ ለሁሉም አፍሪካውያን ከቪዛ ነፃ የጉዞ ፈቃድ ይፋ አደረገች።

63

ባሕርዳር፡ ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ርዋንዳ ለሁሉም አፍሪካውያን ከቪዛ ነፃ የጉዞ ፈቃድ ይፋ አድርጋለች።

እንደ አውሮፓ የሼንገን ዞን የሰዎችን በነፃነት መንቀሳቀስ እና መገበያየት ለማሳደግ አሕጉሪቱ የያዘችውን ዓላማ ተከትሎ ርዋንዳ አፍሪካውያን ያለ ቪዛ ወደ ሀገሯ እንዲገቡ መፍቀዷን በትናንትናው ዕለት አስታውቃለች።

ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ከቪዛ ነፃ የጉዞ ፈቃዱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት፤ እምቅ አቅም ያላትና የቱሪዝም መዳረሻ የሆነችው አፍሪካ 60 በመቶው ከአፍሪካ ውጭ ባሉ ጎብኚዎች ጥገኛ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን መረጃ እንደሚያሳይ ጠቅሰዋል፡፡

ካጋሜ በ23ኛው የዓለም የጉዞ እና ቱሪዝም ምክር ቤት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ማንኛውም አፍሪካዊ በፈለገ ጊዜ ወደ ርዋንዳ በአውሮፕላን መግባት እንደሚችልና ምንም አይነት ክፍያ እንደማይከፍልም ገልፀዋል።

“የራሳችንን አሕጉራዊ ገበያ መዘንጋት የለብንም” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ “በመጪዎቹ አስርት ዓመታት መካከለኛ አቅማችን በፍጥነት ማደጉን ከቀጠለ አፍሪካውያን የዓለም አቀፉ ቱሪዝም የወደፊት እጣ ፈንታ ይሆናሉ” ብለዋል፡፡

በዚህም ርዋንዳ ለአፍሪካውያን የጉዞ ገደቦችን በማንሳት አራተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ትሆናለች ማለታቸውን ኢንዲፔንደንት ዘግቧል።

ጋምቢያ፣ ቤኒን እና ሲሼልስ ሌሎቹ ከቪዛ ነፃ የጉዞ ፈቃድ የሚሰጡ ሀገራት ናቸው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleገብረመድን ኃይሌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ኾነው ተሾሙ።
Next article“የሕዝብ ጥያቄዎችን ፈጥኖ በመፍታት ለግጭት የሚዳርጉ ክፍተቶችን መዝጋት ይገባል” የባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች