ገብረመድን ኃይሌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ኾነው ተሾሙ።

37

ባሕር ዳር: ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)አሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ ዋልያዎችን ለማሠልጠን የአንድ ዓመት ውል ተፈራርመዋል።

250ሺህ ብር የተጣራ ወርሃዊ ደሞዝም ይከፈላቸዋል ብሏል ፌዴሬሽኑ በሰጠው መግለጫ።

በቀጣይ በሚደረጉ የአፍሪካና የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ጠንካራና ተፎካካሪ ብሔራዊ ቡድን መገንባት ለአሠልጣኙ እንደ ግዴታ መቀመጡንም የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሐፊ ባሕሩ ጥላሁን ተናግረዋል።

አሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ ባላቸው አቅምና የተጫዋቾች ጥራት ልክ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

በብሔራዊ ቡድኑ ወጣቶች እድል በሚያገኙበት መንገድ ላይም ትኩረት እንደሚያደርጉ ነው ያብራሩት።

አሠልጣኙ የመጀመሪያ የብሔራዊ ቡድን ጨዋታቸውን ከ12 ቀን በኋላ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከሴራሊዮን ጋር ያደርጋሉ።

አሠልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ በኢትዮጵያ መድን አሠልጣኝነታቸው ጭምር እንደሚቀጥሉም ተነግሯል።

ከአሠልጣኝ ውበቱ አባተ ስንብት በኋላ ብሔራዊ ቡድኑ የፌዴሬሽኑ ቴክኒካል ዳይሬክተር በኾኑት ዳንኤል ገብረማርያም ሲመራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ዘጋቢ፡- ባዘዘው መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleዛሬ በሊጉ የጣና ሞገዶቹና የአጼዎቹ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።
Next articleርዋንዳ ለሁሉም አፍሪካውያን ከቪዛ ነፃ የጉዞ ፈቃድ ይፋ አደረገች።