“የሀገራችንን የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለማጽናት በዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ላይ ጠንክሮ በመሥራት ያስፈልጋል” መለስ ዓለሙ

171

አዲስ አበባ: ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የብልጽግና ፓርቲ በዲሞክራሲ ባሕል ግንባታ ላይ ያተኮረ ውይይት ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ ከሲቪክ ማኅበራት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እያካሄደ ነው።

በውይይቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የሲቪክ ማኅበራት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ዘርፍ ኀላፊ መለስ ዓለሙ “የሀገራችንን የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለማጽናት በዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ላይ ጠንክሮ በመሥራት ያስፈልጋል” ሲሉ አስገንዝበዋል።

አካታች የፖለቲካ ተሳትፎና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት ማኅበረሰቡ የሠለጠነ የዴሞክራሲ ግንባታ ባሕልን እንዲያዳብር የሚያስችል ስለመኾኑም አንስተዋል።

በዴሞክራሲ ባሕል ግንባታ ላይ የባለድርሻ አካላት ሚናን የተመለከተ የመነሻ ሀሳብ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግም ተገልጿል።

ዘጋቢ:- ቤተልሄም ሰለሞን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሕዝብ የሚያነሳቸው ጥያቄዎችን መለየት ፣ ማደራጀትና እንዲፈጸሙ መከታተል የማይታለፍ የወቅቱ ተግባር ነው” የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር
Next articleበአማራ ክልል የሚታረሰው ለም መሬት በአፈር አሲዳማነት እየተፈተነ እንደሚገኝ የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ።