“ሰላማችንን ለማጽናት የሁሉም ተሳትፎ ያስፈልጋል” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው

63

ባሕር ዳር: ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች በወቅታዊ ኹኔታና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ነው።

በውይይቱ መልእክት ያስተላለፉት የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው በክልሉ የተፈጠረው ችግር አሁን ያለበትን ኹኔታ የምናይበትና የቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሚቻልበት ውይይት መኾኑን ተናግረዋል።

“ሰላማችን ለማጽናት የሁሉም ተሳትፎ ያስፈልጋል” ብለዋል። እያንዳንዱ ሰው የሰላም ባለቤት መኾኑን ያነሱት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ሁሉም ለሰላም አስተዋጽኦ ሊያደርግ እንደሚገባ ገልጸዋል። በሰላም እጦት ምክንያት የተቀዛቀዘውን ልማት ለማነቃቃት ውይይቱ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም ተናግረዋል።

አሁን ያለው የአኮኖሚ መቀዛቀዝ ከቀጠለ የበለጠ ጉዳት የሚከሰትበት ፣ የኑሮ ውድነት የሚጨምርበት ፣ የምጣኔ ሃብት ውድቀት የሚታይበት ይኾናል ነው ያሉት።

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በምጣኔ ሃብት የተሻለ ለመኾን ሰላምን እየጠበቁ መሥራት ይገባልም ብለዋል።

የመልካም አሥተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ውይይት እንደሚደረግባቸውም አመላክተዋል። ከሕዝብ ጋር በተሠራው ጠንካራ ሥራም ከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ መኾኗንም ተናግረዋል።

በውይይቱ የከተማዋ ተዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ፣ የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ኀላፊ ሲሳይ ዳምጤን ጨምሮ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለክብራቸው መታሰቢያ፣ ለታሪካቸው መዘከሪያ”
Next articleአስፈላጊውን የሰው ኃይል በማሟላት የጸረ ሙስና ትግሉን አጠናክሮ ለማቀጣጠል እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል የጸረ ሙስና ኮሚቴ አስታወቀ፡፡