
ባሕር ዳር: ጥቅምት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ከ15 ዓመት በታች ወንዶች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ውድድር ላይ ለመካፈል ወደ ዩጋንዳ አቀንቷል።
ውድድሩ በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ከጥቅምት 24 እስከ ህዳር 6 ይካሄዳል። የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ውድድር ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ታዳጊ ቡድን በምድብ ሀ ከአስተናጋጇ ዩጋንዳ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ጅቡቲ እና ደቡብ ሱዳን ጋር ተደልድሏል። ዛሬ ለውድድሩ ቡድኑ ወደ ዩጋንዳ ጉዞ መጀመሩን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!