
ባሕር ዳር: ጥቅምት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ለ29ኛ ጊዜ የሚደረገው የአፍሪካ የአመቱ ኮከቦች ምርጫ እ.ኤ.አ ታህሳስ 11 በሞሮኮ ማራካሽ ይከናወናል።
ካፍ ለዓመቱ ኮከቦች ምርጫ 30 እጩዎችን ይፋ አድርጓል።
በ2023 የኳታር ዓለም ዋንጫ ዓለምን ያስገረመው የአህጉሩ ምርጥ ብሔራዊ ቡድን ሞሮኮ 7 ተጫወቾችን በማስመረጥ ቀዳሚ ሆኗል።
አልጀሪያ፣ ካሜሩን፣ ሴኔጋል፣ ኮትዲቯርና ጋና እያንዳንዳቸው ሁለት ተጫዋቾችን አስመርጠዋል።
ቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒ፣ ማሊ፣ ናሚቢያ፣ ናይጀሪያ፣ ደቡብ አፍሪካና ቱኒዚያ ደግሞ አንድ አንድ ማስመረጣቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።
ያለፈው ሽልማት አሸናፊ ሳዲዮ ማኔ፣ ሙሀመድ ሳላህና ሪያድ ማህሬዝ ያአሸናፊነት ቅድመ ግምት አግኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!