የሰላም እና የፀጥታ ችግሮች በምክክር እንዲፈቱ እና መደበኛ የልማት ሥራዎች እንዲቀጥሉ የፋርጣ ወረዳ ነዋሪዎች ጠየቁ።

53

ባሕር ዳር: ጥቅምት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በደቡብ ጎንደር ዞን የፋርጣ ወረዳ አስተዳደር በወቅታዊ የሰላምና የጸጥታ ችግሮች ዙሪያ ከተለያዩ የማኅረሰብ ክፍሎች ጋር የውይይት መድረክ አካሄዷል
በውይይት መድረኩ ላይ የአካባቢው ማኅበረሰብ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር ሕግ የማስከበር ሥራ በመሥራቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የአካባቢው ሰላም እየተሻሻለ መጥቷል ተብሏል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች ወቅታዊው የሰላም እና የጸጥታ ችግር በምክክር እንዲፈታ እና መደበኛ የልማት ሥራዎች ሳይደናቀፍ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

መረጃው የፋርጣ ወረዳ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በቃል ኪዳን የተሰጠች፤ በነጻነት የኖረች”
Next articleየ2023 የአፍሪካ እጩ ኮከብ ተጫወቾች ይፋ ኾኑ።