የሲቢኢ ኑር ከወለደ ነጻ የባንክ አገልግሎት ራሱን የቻለ የመንግሥት ባንክ እንዲኾን የባንኩ የሼሪዓ አማካሪ ምክር ቤት አባላት ጠየቁ።

62

አዲስ አበባ: ጥቅምት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ባንኩ የተሟላ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ሥራ የጀመረበትን 10ኛ ዓመት ክብረ በዓል እያከበረ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ የሲቢኢ ኑር ከወለደ ነጻ የባንክ አገልግሎት ተጨማሪ አማራጭ የቀረበ ሲኾን አመርቂ ስኬት ተገኝቶበታል ብለዋል።

በ10 ዓመታት ጉዞ ውስጥ የነበሩትን ስኬቶችን እና ወጣ ውረዶችን መዘከር የተፈለገው ዘርፉን ለማዘመን እና የተሣካ አገልግሎት ለማቅረብ ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት የሼሪዓ ሕግን የተከተለ የሲቢኢ ኑር ከወለደ ነጻ የባንክ አገልግሎት ራሱን የቻለ የመንግሥት ባንክ እንዲኾን የቦርድ አመራር እና የባንኩ የሼሪዓ አማካሪ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ የኾኑት ሼህ መሃመድ ሀሚዲን (ዶ.ር) ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ምክትል ፕሬዚዳንት ኑሪ ሁሴን የተሟላ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቱ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን የበርካታ ዓመታት ጥያቄ የመለሰ አገልግሎት እንደኾነ ጠቅሰዋል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት ትርፍ እና ኪሳራን የሚጋራ የአገልግሎት ዓይነት መኾኑንም አስረድተዋል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንት ኑሪ ሁሴን ባንኩ 98 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ በዘርፉ ሠፊ ሥራ የተሠራ ቢኾንም አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ አሁንም ብዙ እርምጃዎችን መጓዝ እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት በ1 መቶ 53 ራሱን የቻለ ቅርንጫፎች እና በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በአንድ መስኮት አገልግሎት እየሠጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የሼሪዓ ሕግን የተከተለ የሲቢኢ ኑር ከወለደ ነጻ የባንክ አገልግሎት የጀመረበት 10ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የተለያዩ መርሐ ግብሮች እንደሚኖሩ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት የሼሪዓ ሕግን የተከተለ የሲቢኢ ኑር ከወለደ ነጻ የባንክ አገልግሎት ራሱን የቻለ የመንግሥት ባንክ እንዲኾን የባንኩ የሼሪዓ አማካሪ አባላት ጠይቀዋል።

ዘጋቢ፡- ዳንኤል መላኩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሦስት ወራት ከዳያስፖራው ከ745 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ ተሰብስቧል” የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት
Next article“ታሪክ የማያቋርጥ ክስተት እስከኾነ ድረስ የግጭት መንስዔ ሊኾን አይገባም” አሰፋ ባልቻ (ዶ.ር)