
ባሕር ዳር: ጥቅምት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ሦስት ወራት ከዳያስፖራው ከ745ሺ ዶላር በላይ ድጋፍ መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታውቋል።
አገልግሎቱ እንደገለጸው በበጀት ዓመቱ ሩብ ዓመት በሬሚታንስና በኢንቨስትመንት የተገኘውን ሀብት ሳይጨምር ከ745 ሺህ በላይ ዶላር ድጋፍ ተልኳል፡፡
ለዓባይ ግድብ ከቦንድ ሽያጭ ፣ ከስጦታና ከልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ከ93 ሺህ ዶላር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል፡፡
ለገበታ ለትውልድ ፕሮጀከትም ከ163 ሺህ ዶላር በላይ ማሰባሰብ መቻሉም ተገልጿል።
ለልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎች ከ488 ሺህ ዶላር በላይ በጥሬ ገንዘብና በአይነት ድጋፍ መገኘቱን ኢፕድ ዘግቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!