“ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም ግንባታ የትምህርት ዘመኑ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ነው” ትምህርት ቢሮ

51

ጎንደር: ጥቅምት 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ዘመኑን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም እየገመገመ ነው። በተጨማሪም በቀጣይ ጊዜያት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር በጎንደር ከተማ ውይይት እያካሄደ ነው።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኀላፊ እየሩስ መንግሥቱ የሩብ ዓመት አፈጻጸም እና የቀጣይ ጊዜያትን አቅጣጫዎችን ለተሳታፊዎች እያቀረቡ ነው።

ምክትል ቢሮ ኀላፊዋ “ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም ግንባታ የትምህርት ዘመኑ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ነው” ብለዋል። በተጨማሪም የትምህርት አሥተዳደር እና መሰረተ ልማት ዝርጋታ፤ የትምህርት እና ሥልጠና አግባብነት ጥራት እና ፍትሐዊ ተደራሽነት ትኩረተት ተሰጥቷቸው እየተሠሩ ነው ተብሏል።

የጎልማሶች እና መደበኛ ያልኾነ ትምህርት፣ የትምህርት ምዘና እና አገልግሎት እና የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት የስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች ትኩረት መኾናቸው ተነስቷል።

ዘጋቢ፦ ቃልኪዳን ኃይሌ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ወራት ስኬታማ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ሠርታለች” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
Next articleአቶ አደም ፋራህ በጅቡቲ ኦልድ ፖርት ተገኝተው የ2016/17 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ የማጓጓዝ ሂደትን አበሰሩ።