
ባሕር ዳር: ጥቅምት 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ጋር ተወያይተዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የተላከ መልዕክትም ለፕሬዝዳንቱ አድርሰዋል።
መሪዎቹ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን በሁለትዮሽ፣ በባለብዙ ወገን እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል።
ሁለቱን ሀገራት በመሰረተ ልማት ለማስተሳሰር ጠንካራ የትብብር ሥራ ለመስራት ከስምምነት ደርሰዋል።
በሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች መካከል ያለው የሕዝብ ለሕዝብ መስተጋብር ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም ምክክር አድርገዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ጋር የነበረቻውን ውይይት ከጨረሱ በኋላ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጀምስ ሞርጋን ጋር የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!