“ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ አገልግሎትን ማስፈን የዕድገትና ሥልጣኔ ምልክት ነው” የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር

40

አዲስ አበባ: ጥቅምት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት እና ተጠሪ ተቋማት የ2016 በጀት ሩብ ዓመት አቅድ አፈጻጸምን እየገመገሙ ነው።

አፈጻጸሙን ያቀረቡት በጽሕፈት ቤቱ የጥራትና ትግበራ ዳይሬክተር ሙሉነህ ሙሉጌታ ናቸው፡፡ ዳይሬክተሩ ባቀረቡት የአፈጻጸም ሪፖርት እንዳሉት:-

✍️ቅንጅታዊ አሠራርን ማጎልበት

✍️የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት ማደስ

✍️ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ቅሬታዎችን በአግባቡ ለመፍታት ጥረት መደረጉን

✍️የከተማ ውበትን ለማስጠበቅ የቆሻሻ ማስነሳት ሥራ መከናዎኑን

✍️የጎብኝዎችን ቁጥር ለማሳደግ ምቹ ኹኔታዎችን የመፍጠር ሥራ ተሠርቷል

✍️ትልልቅ ፕሮጀክቶችን የመከታተልና የመደገፍ ተግባርም ተከናውኗል

✍️የውጭ ኩባንያዎች ወደ ከተማዋ ገብተው እንዲሠሩ ማድረግ እና መሠል ተግባራትን ማከናወን መቻሉን አብራርተዋል።

በሩብ ዓመቱ የታዩ ክፍተቶችን ሲያብራሩም:-

👉ስለከተማ ፅዳት ለኅብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ አለመፈጠሩ

👉የለውጥ ሥራ የአመራር ብቻ ነው ብሎ ማሰብ መኖር

👉የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን በዘላቂነት መፍታት አለመቻል በክፍተት የተለዩ እንደኾነ አንስተዋል።

ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሉሲዎች የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬ በአቡጃ ያደርጋሉ።
Next article“በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚመረተው የቆዳ ምርት ውስጥ ወደ ገበያ የሚቀርበው ግማሹ ብቻ ነዉ” የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር