ሉሲዎች የመልስ ጨዋታቸውን ዛሬ በአቡጃ ያደርጋሉ።

21

ባሕር ዳር:ጥቅምት 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በ2024 ኦሎምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ከናይጀሪ ጋር ይካሄዳል።

ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ እንደሚያመለክተው ጨዋታው ምሽት12 ሰዓት ላይ በአቡጃ አቢዮላ ስታዲየም ይደረጋል። ሉሲዎቹ የመልስ ጨዋታቸውን ለማድረግ ከቀናት በፊት አቡጃ ገብተዋል። ልምምዳቸውንም በሞሽድ አቢዮላ አለም ዓቀፍ ስታዲየም ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በአዲስ አበባ በተደረገው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች አንድ አቻ በኾነ ውጤት ማጠናቀቃቸው ይታወሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የከተማዋ ነዋሪዎች መብታቸውን በልመና እና በግዥ ማግኘት የለባቸውም” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው
Next article“ጥራት ያለው እና ቀልጣፋ አገልግሎትን ማስፈን የዕድገትና ሥልጣኔ ምልክት ነው” የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር