በአማራ ክልል በመኸር ከአምስት ሚሊየን ሔክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

46

ባሕር ዳር: ጥቅምት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የ2016 የምርት ዘመን አንደኛ ሩብ ዓመት ግምገማ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በከሚሴ ከተማ በማካሄድ ላይ ነው።

የክልል፣ የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም የግብርና ቤተሰብ በተገኙበት የ2016 አንደኛ ሩብ ዓመት ግምገማ በማካሄድ ላይ ነው።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኅላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) እንዳሉት በክልሉ በመኽር ከ5 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል። 160 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በክልሉ የዝናብ እጥረት ከገጠማቸው አካባቢዎች ውጭ ሁሉም የተሻለ የሰብል ቁመና የታየበት ዓመት መሆኑንም ተናግረዋል።

እንደ አጠቃላይ የምስራቅ አማራ ዞኖችን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ሥራዎች በመገምገም በመኽር ሥራ እንቅስቃሴ የቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጡም ተናግረዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ አዲሱ ቡላ በበኩላቸው በብሔረሰብ አስተዳደሩ 2015/16 የመኽር ግብርና እንቅስቃሴ 59 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል ብለዋል።

15 ሺህ ሄክታር መሬት በክላስተር ለማልማት ታቅዶ አፈጻጸሙ ከ90 በመቶ በላይ ለመፈጸም ተችሏል ነው ያሉት።

በዞኑ የበጋ መስኖ ስንዴ ላይ 714 ሄክታር መሬት በዘር እንደሚሸፈንም አቶ አዲሱ ቡላ መናገራቸውን የዞኑ ኮምዩኒኬሽን መምሪያ ገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከቅርጫት ኳስ ኮከብነት ወደ ቢሊየነርነት፡፡
Next article“ሰላም ከሌለ ምርትን ከቦታ ቦታ ማዘዋወር ስለማይቻል አምራቹም ኾነ ተጠቃሚው ተጎጂ ነው” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)