
ባሕር ዳር: ጥቅምት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የቀድሞው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ማጂክ ጆንሰን የፎርብስ መጽሔት ያላቸው ሀብት የቢሊየነርነት ደረጃ ላይ እንዳስቀመጣቸው አስነብቧል፡፡
መጽሔቱ የጆንሰንን የሀብት መጠን 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን አስታውቋል።
ጆንሰን በተለያዩ የስፖርት ክለቦች ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ እንዳለው ያተተው ቢቢሲ በተለያዩ ኩባንያዎች ውስጥም መዋለ ንዋዩን እያፈሰሰ የሚገኝ ባለሀብት መኾኑን አስታውሷል፡፡
በሕይወት የኢንሹራንስ ኩባንያ ውስጥም ከፍተኛ ድርሻ አለው ትግል ብሏል፡፡
የ64 ዓመቱ ጆንሰን እ.ኤ.አ በ1996 ከቅርጫት ኳስ ስፖርት ማኅበር ራሱን ከማግለሉ በፊት በአሜሪካ ብሔራዊ የቅርጫት ኳስ ማኅበር ውስጥም ስመ ጥር ነበር፡፡
ይሁንና አብዛኛውን ሀብት የሰበሰበው ከስፖርት ዘርፍ ውጭ እንደኾነም ተጠቁሟል።
ጆንሰን ከስፖርቱ ዘርፍ የሰበሰበው የገንዘብ መጠን 40 ሚሊዮን ዶላር ብቻ እንደኾነም መጽሔቱ አትቷል።
ግለሰቡ በስታር ባክስ ፣ በበርገር ኪንግ ፣ በመገናኛ እና በሕይወት ኢንሹራንስ ኩባንያ ዘርፎችም ገንዘቡን ፈሰስ እያደረገ ይገኛል፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!