
ባሕር ዳር: ጥቅምት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የቀድሞው የስፔን እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዝዳንት ሉዊስ ሩቢያሌስ ለሦስት ዓመታት ያህል ቅጣት ተላለፈባቸው።
የስፔን ሴቶች ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ እንግሊዝን ሲያሸንፍ ሩቢያሌስ የፊት አጥቂዋን ጄኒ ሄርሞሶን ያለፍላጎቷ መሳማቸው ነው ለክስ ያበቃቸው።
በዚህም መሠረት የዓለም እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ግለሰቡን በጊዜያዊነት ለ90 ቀናት እገዳ ጥሎባቸው ቆይቷል ፤ጉዳዩን በጥልቀት ሲመረምርም ቆይቷል፡፡
በመጨረሻም ሉዊስ ሩቢያሌስ የፊፋን የዲሲፕሊን ሕግ አንቀፅ 13 ን መጣሳቸው በመረጋገጡ ለፈጸሙት አስነዋሪ ድርጊት ለሦሥት ዓመታት ከማንኛውም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲታገዱ ቅጣት እንደተጣለባቸው ቢቢሲ ዘግቧል።
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!