ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን ለተጠቃሚዎች እያስተዋወቀ መኾኑን የደብረ ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል ገለጸ።

60

ባሕርዳር፡ ጥቅምት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል በተያዘው በጀት ዓመት ከ2 መቶ በላይ የምርምር ሥራዎችን በማከናወን የግብርና ልማቱን ለማፋጠን እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

ማዕከሉ በቴክኖሎጂ፣ በደን ልማት፣ በአፈርና ውኃ፣ በመኖና ሥነ አመጋገብ ዘርፍ፣ በእንስሳት ዝርያ ብዜትና ማሻሻል፣ በሰብል ምርምር እንዲሁም በማኅበራዊ ምጣኔ ሃብትና ቴክኖሎጂ ሥርፀት ዘርፎች የምርምር ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

ለአካባቢው ስነምህዳር ተስማሚ የሆኑ፣ የምርታማነት ደረጃቸው የተሻሻሉና ተጽዕኖን መቋቋም የሚችሉ ምርጥ ዘሮችን በማባዛትም አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረጉ ተመላክቷል።

ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን ለተጠቃሚው በማቅረብና በማስትታወቅ ረገድ 12 ልዩ ልዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለ 4 መተ 48 አርሶ አደሮች ተደራሽ ማድረጉንም የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶክተር አዕምሮ በዛብህ ገልጸዋል።

ማዕከሉ ለበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መፋጠን አስተዋጾ ያላቸውን የምርምር ሥራዎች እያወጣ፣ እያባዛና ለተጠቃሚው ማኅበረሰብ እያስተዋወቀ እንደሚገኝም ተመላክቷል።

የግብርና ምርታማነትን እንዲሁም የንጥረ ምግብ ይዘትን ማሻሻልና ለፋብሪካ ግብዓት ጥራት ያላቸው ምርቶችን ማስገኘት በዘርፉ ትኩረት ከተሠጣቸው ተግባራት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

ዶክተር አዕምሮ እንዳሉት ታዲያ በቀጣይም ማዳቀልን መሠረት ባያደረገ መልኩ የተጀምሩ ተግባራት ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል ብለዋል።

የደብረ ብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል ያወጣቸውን፣ ያስተዋወቃቸውንና ያባዛቸውን የምርምርና የቴክኖሎጂ ሥራዎች በመስክ ምልከታ ለባለድርሻ አካላት አስተዋውቋል።

በደጀኔ በቀለ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበበጀት ዓመቱ ከውዝፍ ግብር 27 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ማቀዱን የደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ።
Next article“ወረቀት ላይ የተቀመጠውን እቅድ ወደ ገንዘብ ለመቀየር የሁሉንም ተሳትፎ ይጠይቃል” የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ