
ደሴ: ጥቅምት 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ድምጻዊ ዓባይነህ ደጀኔ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሰርግ ሙዚቃን በሸክላ ያስቀረጹ አንጋፋ አርቲስት ነበሩ።
የቀድሞው የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራ ቡድን አባል የነበሩት የድምጻዊ ዓባይነህ ደጀኔ የሰርግ ሙዚቃ ሲነሳ ስማቸው አብሮ ይነሳል፡፡
በተለይ በ1964 ዓ.ም በሀገረ ሆላንድ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ የሰርግ ሙዚቃን በሸክላ አስቀርጸዋል፡፡
“አንቺ ቆንጆ ጽጌረዳ የበርሃ ሎሚ” የተሰኘው ሙዚቃ ዘመን የማይሽረው የድምጻዊው ሥራ ነው።
ድምጻዊ ዓባይነህ ደጀኔ በ1955 ጀምረው እስከ 1983 ዓ.ም በሙዚቃው ዓለም አሳልፈዋል፡፡ ድምጻዊ ዓባይነህ ደጀኔ በኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከቀን ሠራተኝነት የሥራ መስክ ተነስተው እስከ ኤሌክትሪሽያንነት ድረስም አገልግለዋል፡፡
ለዓመታት ደግሞ በሚኒ ሚዲያ ባለሙያነት ማገልገልም ችለዋል፡፡
በ1940 ዓ.ም የተወለዱት ድምጻዊ ዓባይነህ ደጀኔ በ76 ዓመታቸው ዛሬ ጥቅምት 19/2016 ዓ.ም አርፈዋል፡፡
ዘጋቢ፦ ደጀን አምባቸው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!