የቱሪዝም መዳረሻዎች የጉብኝት ዋጋ መሻሻሉን የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

49

ባሕር ዳር:- ጥቅምት 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ በአማራ ክልል ምክር ቤት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የቱሪዝም መዳረሻ ክፍያ ማሻሻሉን የቢሮ ኃላፊው ጣሂር ሙሐመድ ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት የነበረው የጎብኝዎች ክፍያ ለረጅም ዓመታት የቆየ እና ወቅቱን ያገናዘበ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል። ይህ የቆየ ክፍያ ምክንያታዊ ማስተካከያ ሳይደረግለት በመቆየቱ ለሕገ ወጥነት መስፋፋት ምክንያት እንደሚኾነም አሳውቀዋል።

ይህንን ታሳቢ በማድረግ የመዳረሻዎችን ዋጋ ለማሻሻል ጥናት ተደርጓል፤ በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት ተከናውኗል። በዚህ መሠረት ተማሪዎችን፣ መደበኛ ጎብኝዎችን፣ የውጭ ዜጎችን እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎችን አቅም ታሳቢ ያደረገ እና ሁሉንም ተጠቃሚ ያደረገ ማሻሻያ መደረጉን አሳውቀዋል። አንዳንድ ዘርፎች ላይ የነበረው ታሪፍ እንዲቀጥል መደረጉንም አንስተዋል።

ማሻሻያው የመዳረሻዎችን ባሕሪ ታሳቢ ያደረገ እና የጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ በሚያራዝም መንገድ መሠራቱን ነው ቢሮ ኃላፊው የገለጹት።

ዘጋቢ:- ዳግማዊ ተሠራ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሁለተኛው የግብርና ዕድገት ፕሮግራም ውጤት ላስመዘገቡ ክልሎችና ለመልካሳ ግብርና ምርምር ድጋፍ ተደረገ፡፡
Next article“በደሴ ከተማ ለፍትሕ የቆመ ችሎት”