
ባሕር ዳር: ጥቅምት 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት “ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሀሳብ ሥልጠና መሰጠት ተጀመረ።
በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እየተሰጠ የሚገኘው ሥልጠና ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
በሥልጠና ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጨምሮ የምክር ቤቱ የሥራ ኃላፊዎችና አባላት ተገኝተዋል።
ኢዜአ እንደዘገበው በሥልጠናው ሀገራዊ፣ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ የሰላም፣ የልማትና ሌሎች ጉዳዮችን መነሻ ያደረጉ ጹሑፎች ቀርበው ምክክር ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!