
ባሕር ዳር: ጥቅምት 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በእግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት ተጠብቆ የነበረው የኤል ክላሲኮ ጨዋታ በሪያል ማድሪድ አሸናፊነት ተጠናቋል
በስፔን ላሊጋ ባርሴሎናን ከሪያል ማድሪድ ያገናኘው ጨዋታ በማድሪድ የበላይነት ተጠናቋል።
ባርሴሎና የመጀመሪያውን የጨዋታ አጋማሽ አንድ ለባዶ በኾነ ውጤት እየመሩ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተው ነበር። ነገር ግር ሎስ ብላንካዎቹ ከእረፍት መለስ ሁለት ግቦችን አስቆጥረው ተጠባቂውን ጨዋታ ማሸነፍ ችለዋል።
እንግሊዛዊ ጁዲ ቤሊንግሃም የማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች በማስቆጠር በነጮቹ ቤት መድመቁን ቀጥሏል።
የባርሴሎናን ብቸኛ ግብ ደግሞ ጀርመናዊ ጉንዱጋን ነው ያስቆጠረው።
ዘጋቢ፦ አስማማው አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!